חיפוש באתר

קול קורא לפסטיבל נווה יוסף ה-14

የ-14 ኛው የንቬ ዮሴፍ ፌስቲቫል የመሳተፊያ ጥሪ

የንቬ ዮሴፍ ማህበረሰባዊ ቲያትር ፌስቲቫል: የማህበረሰብ ቲያትር
ቡድኖችንና የቲያትር ተማሪዎችን በ2019 የንቬ ዮሴፍ ፌስቲቫል
ለመሳተፍ ሃሳባችሁን በቅድመ ምዝገባ እንድታቀርቡ ያስታውቃል::

 

ይህ ጥሪ ለመላው የማህበረሰብ ቲያትር ዳይሪክተሮች: ተጫዋቾች እና ተማሪዎች
ሲሆን: በአገር አቀፍ ሰፊ እና በታወቀው ፌስቲባል ተገኝቶ የሙያ ውጤትን ወይም
የስራ ሂደቶችን በቲያትር መሳሪያዎች ከተሳታፊዎች ጋር ለማሳየት ያስችላል::
ፌስቲባሉ ከ 15 እስከ 17 ኦክቶበር 2019 በሱኮት በዓል በምስራቅ ሃይፋ ራቢ ማሻሽ
ጎዳና በሚገኘው የንቬ ዮሴፍ ማትናስ - ኮምዩኒቲ ማእከል ሕንፃዎች ይካሄዳል::

 

የፌስቲባሉ ኪነ-ጥበብ ሥነምግባር ኮሚቴ ትኩረት ከሚያደርገው: በተላያዩ ማህበረሰብ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ትክክለኛ ድምጾችን
ትርጉም ለመስጠት ዓላማ ያላቸው ሃሳቦችን ይቀበላል:: በእስራኤል ማህበራዊ መልዕክቶች እና በባህላዊ ውይይቶች ድምጻቸው
የማይሰሙ ማህበረሰቦችን አቋም የሚያመለክቱ ስራወች: ማህበራዊ መልዕክቶችን ያዘሉ እና በትክክል የማህበረሰባዊ ሂደቶችን መድረክ
ላይ ማንጸባረቅ የሚችሉ ይመረጣሉ:: የዝግጅቱ ዓመታዊ በተጨባጭ ረእሱ ላይ "እኛ ሁሉም የሰው ልጅ ነን" ከሚለው ጥያቄ ጋር
ይዘት ያላቸው ዝግጅቶች ተቀባይነት ይኖራቸዋል፡፡ በተጨማሪም አዲስና የመጀመሪያ ዝግጅት ለሚያሳዩ ስራዎች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡
፡ በተጨማሪም ኮሚቴው የጎዳና ትርዒቶችን ሰሪ ቡድኖች: የተለያዩ የሰርቶ ማሳያ መድረኮች እና በታዳጊ ልጆች ላይ ያተኮሩ ስራዎች
እንደሚፈለጉ ያስታውቃል::
ለፌስቲባሉ ተሳታፊነት ለመመረጥ የበቁ ስራዎች: በፌስቲባሉ እቅድ በቋንቋቸው እና በአስተያየታቸው በዕብራይስጥ: በአረብኛ:
በሩሲያኛ: በአማርኛ እና በልጆች መሰረት ይመደባሉ::
የፌስቲባሉ ኪነ-ጥበብ ገምጋሚ ኮሚቲ በሂደቱ መጨረሻ ሶስት ሽልማቶችን ያበረክታል:- ልዩ የስነ-ጥበብ ቋንቋ ሽልማት: ለቡድን
ስራ ሽልማት እና ለመድረክ ግጥሚያ አፈፃፀም ሽልማት ይሰጣል: በተጨማሪም የገምጋሚውን ህዝብ ርካታ የሚገልጽ ሽልማት ይሰጣል፡፡
ፌስቲባሉ ለማህበረሰብ ባለሙያዎች አዳራሾችን: መድረኮችን: መብራቶችን እና ሳውንድ: እንዲሁም የሎጂስቲክ ድጋፍን እና
የተለያዩ ማበልፀጊያ ግንኙነቶችን ከተለያዩ የማህበረሰብ ማሰልጠኛ መስክ ውስጥ ካሉ ሌሎች የትያትር አለም ሰወች ጋር ያገናኛል::
በፌስቲቫሉ ተቀባይነት ያገኙ ቡድኖች እንደፍላጎታቸው በሂደቱ በሙሉ ሰፊ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የፌስቲባሉ ኪነ-ጥበብ ሥነምግባር ኮሚቴ ለማህበረሰብ ቲያትር ቡድኖች የፌስቲባሉ ተሳታፊ ለመሆን እስከ እለተ እሁድ ማርስ
31 ቀን 2019 ድረስ መመዝገብ እንደሚቻል ያስታውቃል::
የማኅበራዊ ትያትር ባለሙያ ቡድኖች ራሳችሁን ለውድድር ለማቅረብ በዚህ የኢሜል አድራሻ መመዝገቢያ ፋይል ማግኘት ይቻላል-

 

nyccfestival@gmail.com

 

የተሳካ ማህበረሰባዊ ስራ ይሁንልን

 

ጠበቃ ዮናታን ፕሪዳልናደር
የንቬ ዮሴፍ ማህበረሰባዊ
ማዕከላት አማካሪ ሊቀ መንበር

 

ሽሞን ይፍራኽ
የንቬ ዮሴፍ ማህበረሰባዊ
ማዕከላት ስራ አስኪያጅ

 

ታሊ ኬሬን ላውፈር
የኪነ-ጥበብ ሥነምግባር
ስራ አስኪያጅ

 

ያዕቆብ አምሳለም
የባህል አማካሪ ኮሚቴ

 

ኢሪት በን ሻሎም
የባህል አማካሪ ኮሚቴ

 

 

צרו קשר:
מתנסנט חוגים הצהרת נגישות